ባህር ዳር ከተማ አንድ አማካይ ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል

በኮንፌዴሬሽን ካፕ ሁለተኛ ዙርን ጨዋታውን በቅርቡ የሚያደርገው ባህር ዳር ከተማ አንድ ተጫዋች አስፈርሟል።

ከዚህ ቀደም ወሳኝ የሚባሉ ዝውውሮችን በማጠናቀቅ ወደ ዝግጅት የገቡት የጣና ሞገዶቹ አሁን ደግሞ አንድ አማካይ ማስፈረማቸው ተረጋግጧል። ለአንድ ዓመት ለቡድኑ የሚያቆየውን ዝውውር የፈፀም ደግሞ አባይነህ ፌኖ መሆኑ ታውቋል።

አባይነህ ከዚህ ቀድም በሀዋሳ ከተማ፣ በወልቂጤ ከተማ ሲያሳልፍ ያለፉትን ሁለት ዓመታት ደግሞ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቆይታ ያደረገ በማድረግ ንግድ ባንክ ወደ ሊጉ እንዲያድግ ካስቻሉ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ነበር።