ሻሸመኔ ከተማ ዩጋንዳዊ አጥቂ አስፈርሟል

በሻሸመኔ ከተማ ሦስተኛው የውጪ ዜጋ ፈራሚ የአጥቂ ስሥፍራ ተጫዋች ሆኗል።

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር መርሀግብሩን የፊታችን ዓርብ ወላይታ ድቻን በመግጠም የሚጀምረው ሻሸመኔ ከተማ እስከ አሁን በዝውውሩ ከሀገር ውስጥ እዮብ ገብረማርያም ፣ ቻላቸው መንበሩ ፣ ሙሉቀን ታሪኩ ፣ ታምራት ስላስ ፣ ሔኖክ ድልቢ ፣ አሸብር ውሮ ፣ አቤል ማሞ ፣ አብስራ ሙሉጌታ ፣ ተመስገን ተስፋዬ ፣ ሀብታሙ ንጉሴ እና አባቱ ጃርሶን ወደ ስብስቡ የቀላቀለ ሲሆን ከውጪ ሀገር ደግሞ ዩጋንዳዊውን ግብ ጠባቂው ሳይዲ ኬኒ እና ናይጄሪያዊው አማካይ ሚካኤል ኔልሰንን አስፈርሟል። በዛሬው ዕለት ደግሞ 14ኛ ፈራሚ በማድረግ የዩጋንዳ ዜግነት ያለውን አጥቂ አላን ካይዋን በአንድ ዓመት ውል ስለ መቀላቀላቸው ሶከር ኢትዮጵያ አውቃለች።

የ26 ዓመት ዕድሜ እንዳለው የሚነገርለት ይህ አጥቂ የእግርኳስ ህይወቱን በሀገሩ ክለቦች ሶዋና ፣ ቫይፐርስ እና ያለፉትን ሁለት ዓመታት ደግሞ ኤክስፕረስ በተባለ ቡድን ቆይታን ካደረገ በኀበላ ቀጣዩ መዳረሻው ወደ ሀገራችን መጥቶ ሻሸመኔ ከተማ ሆኗል።