መቻል ናይጄሪያዊ አጥቂ ነገ ወደ ስብስቡ ይቀላቅላል

የ2021/2022 የናይጄሪያ ፕሪሚየር ሊግ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪው መቻልን ነገ ይቀላቀላል።

በርከት ያሉ ውል ያላቸው ተጫዋቾችን በመያዛቸው በዝውውሩ ብዙ ያልተሳተፉት መቻሎች ናይጄሪያዊ አጥቂ ለማስፈረም ስለመቃረባቸው ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።

ቡድኑን ለመቀላቀል ከጫፍ የደረሰው ናይጄሪያዊው ቺጂኦኬ ናምዲ አኩኔቶ  ነው። ለሀገሩ ክለቦች ኤምኤፍኤም ፣ ሰንሻይን ስታርስ ፣ ኸርት ላንድ ፣ ሪቨርስ ዩናይትድ እና የተጠናቀቀውን ዓመት ደግሞ ለኒምባ በመጫወት ያሳለፈው የ 25 ዓመቱ አጥቂ በ 2021/2022 በሪቨርስ ዩናይትድ ቆይታው በ 36 ጨዋታዎች 19 ግቦችን በማስቆጠር የውድድር ዓመቱ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ በመሆን ክለቡንም ቻምፒዮን ማድረግ ችሏል። ተጫዋቹ ነገ ሌሊት አዲስአበባ የሚገባ ሲሆን በቀጣይ ቀናት ፊርማውን እንደሚያስቀምጥ ይጠበቃል።