ሻሸመኔ ከተማ የመጨረሻ ተጫዋቹን አስፈረመ

የፕሪምየር ሊግ ጨዋታውን በትላንትናው ዕለት ማድረግ የጀመረው ሻሸመኔ ከተማ የመጨረሻ ተጫዋቹን አግኝቷል።

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ2016 የውድድር ዘመን ተሳትፎውን በትናንትናው ዕለት የጀመረው እና በወላይታ ድቻ ሽንፈት ያስተናገደው ሻሸመኔ ከተማ በክረምቱ የዝውውር መስኮት የመጨረሻውን ፈራሚ አግኝቷል። ምንተስኖት ከበደ ደግሞ ክለቡን የተቀላቀለ ተጫዋች ሆኗል።

በመሐል ተከላካይነት በኢትዮጵያ ቡና ፣ መቻል ፣ መቐለ 70 እንደርታ እና ሲዳማ ቡና የተጫወተው የተከላካይ ስፍራ ተጫዋቹ ቀጣዩ መዳረሻው ሻሸመኔ ከተማ ሆኗል።