ወልቂጤ ከተማ የመሐል ተከላካይ አስፈርሟል

ሠራተኞቹ የተከላካይ ስፍራ ተጫዋች ወደ ስብስባቸው ቀላቅለዋል።

በአሰልጣኝ ሙለጌታ ምህረት እየተመሩ በይበልጥ አዳዲስ እና እንዲሁም ነባር ተጫዋቾችን በመያዝ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን በሀዋሳ ሲሰሩ የነበሩት ወልቂጤ ከተማዎች የመጨረሻ ፈራሚያቸው የመሐል ተከላካዩ ወንድማገኝ ማዕረግ ሆኗል።

በሀዋሳ ከተማ የወጣት ቡድኖች ውስጥ በመጫወት ካሳለፈ በኋላ ለዋናው ቡድን ከስድስት ዓመታት በላይ በመጫወት ያሳለፈው ይህ ተከላካይ የተጠናቀቀውን ዓመት በአንፃሩ በኢትዮ ኤሌክትሪክ ቆይታን አድርጎ በእግር ኳስ ህይወቱ ሦስተኛ ክለቡ የቀድሞው አሰልጣኙ የሚመሩት ወልቂጤ ሆኗል። ክለቡም የመጀመሪያ የሊግ ጨዋታውን በነገው ዕለት ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ያከናውናል።