ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ የሚጀመርበት ቀን ታውቋል

የ2016 የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ የዕጣ ማውጣት እና የሚጀመርበት ቀን ይፋ ሆኗል።

በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌድሬሽን አዘጋጅነት በሁለት ምድብ ተከፍሎ በሁለት ከተሞች የሚከናወነው የ2016 የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ የዕጣ ማውጣት ሥነ ስርዓት እና ውድድሩም መቼ እንደሚጀመር የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌድሬሽን አስታውቋል። አስራ ስምንት የማጠጉ ክለቦች ይሳተፉበታል ተብሎ የሚጠበቀው ይህ ውድድር የዕጣ ማውጣቱ መርሀግብር ህዳር 7 እንዲሁም ደግሞ ህዳር 30 ውድድሩ እንደሚጀምር ፌድሬሽኑ ይፋ አድርጓል።