ሻሸመኔ ከተማ አሰልጣኙን በይፋ ሾሟል

አዲስ አሰልጣኝ ለመቅጠር የተስማማው ሻሸመኔ ከተማ በይፋ አሰልጣኙን ሾሟል።

አዲስ አዳጊው ሻሸመኔ ከተማ አሰልጣኝ ዘማርያም ወልደ ጊዮርጊስን አሰልጣኙ አድርጎ ለመሾም ከስምምነት መድረሱን እና በቀጣይ ቀናት ይፋዊ ስምምነት እንደሚፈፅሙ በሰሞኑ ዘገባችን ማሳወቃችን ይታወቃል።

ይህን ተከትሎም ቡድኑን ለቀናት በልምምድ ሜዳ በመገኘት ሲያሰሩ የቆዩት አሰልጣኙ ዘማርያም በዛሬው ዕለት ሁለቱም አካላት በተገኙበት የፊርማ ሥነ ስርዓቱ በፌዴሬሽን በመገኘት የተፈፀመ ሲሆን አሰልጣኝ ዘማርያም እስከ ውድድር ዓመቱ መጠናቀቂያ ድረስ እንደሚቆዩ እና ቡድኑን በሊጉ ማቆየት ትልቁ ስምምነት እንደሆነ አውቀናል። አሰልጣኙ የመጀመርያ ስራቸውንም ዛሬ ምሽት በስድስተኛ ሳምንት ከወልቂጤ ከተማ ጋር በሚያደርጉት ጨዋታ የሚጀምሩ ይሆናል።

አሰልጣኝ ዘማሪያም ከዚህ ቀደም ፋሲል ከነማ፣ ወልድያ፣ ጅማ አባ ጅፋር፣ ድሬደዋ ከተማ፣ ለገጣፎ ለገዳዲ እና ሌሎች ክለቦች ሲያሰለጥኑ መቆየታቸው ይታወሳል።