ወልቂጤ ከተማ የቡድን አባላት ላይ ዝርፊያ የፈፀመው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ውሏል

ዝርፊያ ተፈፅሞባቸው የነበሩት የወልቂጤ ከተማ ቡድን አባላት ንብረታቸውን ማግኘታቸው ታውቋል።

ቀን ላይ ባስነበብነው ዘገባችን የወልቂጤ ከተማ ቡድን አባላት ለዕለቱ ልምምድ ወደ ሜዳ ወጥተው ሲመለሱ የተለያዩ ንብረቶቻቸው እንደተዘረፉ ገልፀን ነበር።

ጉዳዩን ለአዳማ ከተማ ፖሊስ በማሳወቅ
ወደ ፍለጋ የተሰማሩት የቡድኑ አባላት ተሳክቶላቸው ንብረታቸውን እንዳገኙ ተሰምቷል። ወንጀሉን ፈፀመ የተባለው ተጠርጣሪ ከጠፉት ስልኮች በአንዱ ተጠቅሞ መደወሉን ተከትሎ በተደረገበት ክትትል መነሻነት በቁጥጥር ስር ውሏል። በወቅቱ ከአንድ ስልክ ውጪ ቀሪ ንብረቶች የተገኙ ሲሆን ተጠርጣሪውም ተላልፎ ለፖሊስ መሰጠቱ ታውቋል።