የፕሪሚየር ሊጉ የቀጥታ ስርጭት ሽፋን የሚጀምርበት ቀን ታውቋል


የቀጥታ ስርጭት ሽፋን እንደሚያገኙ በተነገሩት ከ12ኛ ሣምንት ጀምሮ የሚደረጉ የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች ላይ የማይተላለፉ አራት ጨዋታዎች እንደሚኖሩ ተረጋግጧል።


የ2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በአዳማ ሣይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጅማሮውን አድርጎ እስከ አሥራ አምስተኛው ሣምንት ድረስ በዛው እንደሚጠናቀቅ መወሰኑ ይታወሳል። ሆኖም ተቋርጦ የነበረው የሱፐር ስፖርት የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ከ12ኛ ሣምንት ጀምሮ እንደሚተላለፍ ቢነገርም ሐሙስ ጥር 16 እና ዓርብ ጥር 17 የሚደረጉ ጨዋታዎች የቀጥታ ስርጭት ሽፋን እንደማያገኙ የተረጋገጠ ሲሆን ከቅዳሜ ጀምሮ የሚደረጉ ጨዋታዎች ግን የቀጥታ ስርጭት ሽፋን እንደሚኖራቸው ታውቋል።

በዚህም

ሐሙስ ጥር 16/2016 ዓ.ም

ኢትዮጵያ መድን 09፡00 ሻሸመኔ ከተማ
መቻል 12፡00 ፋሲል ከነማ

ዓርብ ጥር 17/ 2016 ዓ.ም

ባህር ዳር ከተማ 09፡00 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
አዳማ ከተማ 12፡00 ሃዋሳ ከተማ

የቀጥታ ስርጭት ሽፋን የማይኖራቸው ጨዋታዎች ናቸው።