ሻሸመኔ ከተማ ብሩንዲያዊ የመስመር ተጫዋች አስፈርሟል

ሻሸመኔ ከተማ የብሩንዲ ዜግነት ያለውን የመስመር አጥቂ ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል።

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ እየተወዳደረ የሚገኘው እና ከወራጅ ቀጠናው ለመውጣት በሁለተኛው ዙር የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ላይ እየተካፈለ የሚገኘው ሻሸመኔ ከተማ ከቀናቶች በፊት ስንታየሁ መንግስቱ ፣ ገዛኸኝ ደሳለኝ እና ሙሉጌታ ወልደጊዮርጊስን ወደ ክለቡ የቀላቀለ ሲሆን ከዩጋንዳዊው አጥቂ አለን ካይዋ ጋር ባለመግባባት መለያየቱ የሚወሳ ሲሆን አሁን ደግሞ የብሩንዲ ዜግነት ያለውን የቀኝ መስመር ተጫዋች የሆነውን አልፍሬድ ኑኩሩንዚዛን ማስፈረሙን ክለቡ ለሶከር ኢትዮጵያ አስታውቋል።

በሀገሩ ክለብ ቡማሙር የከፍተኛ የግብ አስቆጣሪ ሆኖ በመፈፀሙ ወደ ግብፁ ክለብ አልሂተሀድ አሌክሳንድሪያ ከስምንት ወራት በፊት አምርቶ ቆይታን በማድረግ ከወራት በፊት በድጋሚ ተመልሶ በቡማሙር ቆይታን ያደረገው ይህ ተጫዋች ለቀጣዮቹ ወራት በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ቆይታን ለማድረግ ሻሸመኔን በይፋ ተቀላቅሏል።