ኢትዮጵያ መድን ናይጄሪያዊ አጥቂ አስፈረመ

በፕሪምየር ሊጉ ለመቆየት በሁለተኛው ዙር የዝውውር መስኮት በንቃት የተሳተፈው ኢትዮጵያ መድን ናይጄሪያዊ አጥቂ አስፈርሟል።

በፕሪምየር ሊጉ ላይ ደካማ የውድድር ዓመትን እያሳለፈ የሚገኘው የአሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌው ኢትዮጵያ መድን በሊጉ ላይ ለመቆየት በሁለተኛው ዙር የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ሚሊዮን ሠለሞን ፣ ሀይደር ሸረፋ ፣ ተክለማርያም ሻንቆ ፣ አብዲሳ ጀማል እና አቡበከር ሳኒን ያስፈረመ ሲሆን አሁን ደግሞ የመጨረሻ ፈራሚያቸው በማድረግ የናይጄሪያ ዜግነት ያለውን ጄሮም ፊሊፕን ወደ ስብስባቸው ቀላቅለዋል።

1 ሜትር ከ92 ሴንቲ ሜትር የሚረዝመው የፊት መስመር ተሰላፊው ለሀገሩ ክለቦች ጂ ሊች እና ዴሰርት ስታርስ ከተጫወተ በኋላ በመቀጠል ወደ ግብፅ በማምራት በሱዝ ፣ ሶሞሀ ዴክረንስ እና ካናህ በተባሉ ክለቦች ውስጥ በመጫወት አሳልፎ ጥቂት ወራትን ያለ ክለብ ካሳለፈ በኋላ ቀጣዩ መዳረሻው ኢትዮጵያዊው ክለብ ኢትዮጵያ መድን ሆኗል።