በሴቶች ፕሪምየር ሊግ ደደቢት የምድቡ አሸናፊ መሆኑን ሲያረጋግጥ ጌዲኦ ዲላ በአስደናቂ ጉዞው ቀጥሏል

 

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ 16ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬም ሲቀጥሉ ደደቢት የምድብ ሀ አሸናፊ መሆኑን ያረጋገጠበትን ድል አስመዝግቧል፡፡ ጌዲኦ ዲላም በአስደናቂ የውድድር ዘመን ጉዞው ቀጥሏል፡፡

በምድብ ሀ መሪው ደደቢት ከመከላከያ ያደረጉት ጨዋታ በደደቢት 4-0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ ለሰማያዊዎቹ ሎዛ አበራ 3 ግቦች አስቆጥራ ሐት-ትሪክ ስትሰራ ብርቱካን ገብረክርስቶስ ቀሪዋን ግብ አስቆጥራለች፡፡ ድሉን ተከትሎ ደደቢት 43 ነጥቦችን በመሰብሰብ ከተከታዩ አዳማ ከተማ 11 ነጥቦች መራቅ የቻለ ሲሆን 3 ጨዋታዎች እየቀሩት የምድብ ሀ አሸናፊ  መሆኑን አረጋግጧል፡፡

የአምናው ቻምፒዮን ደደቢት በቀጣይ የምድብ ለ አሸናፊ ሆኖ የሚያጠናቅቀውን ክለብ የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ለማንሳት ይጫወታል፡፡

በጨዋታው ሶስት ጎሎችን ያስቆጠረችው ሎዛ አበራ የግብ መጠኗን 29 በማድረስ ለ3ኛ ተከታታይ አመታት ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሆና ለማጠናቀቅ ተቃርባለች፡፡

[table “233” not found /]

የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ – ምድብ ሀ

#ክለብተጫአሸአቻተሸአስተቆልዩነጥብ
13630601141410096
2361791054381660
3361851361441759
436156154356-1351
5361211135052-247
6187472724325
71852111632-1617
81843112245-2315
91813141141-306
10180513847-395

 

በምድብ ለ ወደ አዲስ አበባ የተጓዘው ጌዲኦ ዲላ ዳግም ድል አስመዝግቧል፡፡ ልደታን የገጠመው ጌዲኦ ዲላ 1-0 በመርታት 3ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል፡፡ በሊጉ ዘንድሮ አእየተሳተፈ የሚገኘው ጌዲኦ ዲላ አስደናቂ የውድድር ዘመን ማሳለፉን አሁንም ቀጥሏል፡፡

[table “243” not found /]

የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ – ምድብ ለ

#ክለብተጫአሸአቻተሸአስተቆልዩነጥብ
136276383186587
236207969264367
336158134449-553
436147154453-949
536129153646-1045
6189272521429
71861111933-1419
81851123249-1716
91822141544-298
101821151354-417

Leave a Reply