​ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ዝውውር፡ ጌዲኦ ዲላ

የሴቶች ፕሪምየር ሊግ ዘንድሮ የውድድር ፎርማት ለውጥ በማድረግ በሁለት ዲቪዚዮን ተከፍሎ ይካሄዳል፡፡ በተጠናቀቀው የውድድር አመት በተሳተፈበት የመጀመሪያ አመት ጠንካራ ተፎካካሪ በመሆን ምድብ ለ ን በ3ኛ ደረጃነት ያጠናቀቀውና በአንደኛ ዲቪዝዮን የሚካፈለው ጌዲኦ ዲላም አዳዲስ 5 ተጫዋቾችን በማስፈረም በዲላ ከተማ ዝግጅቱን ማድረግ ጀምሯል፡፡

አዳዲስ ፈራሚዎች

ተከላካዮች፡- ገነሜ ወርቁ (ሲዳማ ቡና)

አማካዮች፡- ቤተልሄም በቀለ (ልደታ)፣ ውሮ ዮሴፍ (ከድሬዳዋ ከተማ)

አጥቂዎች፡- ድንቅነሽ ላቀው (ኢትዮጵያ ቡና)፣ ሳራ ነብሶ (አዲስ አበባ ከተማ) ናቸው፡፡

የጌዲኦ ዲላ የሴቶች ቡድን ከተቋቋመ ከ15 አመት በላይ ቢሆነውም በክለብ ደረጃ ተዋቅሮ በውድድሮች መሳተፍ የጀመረው በ2009 ነበር፡፡ ለዚህ ክለብ መቋቋም ዋንኛ አስተዋፅኦ ያደረጉት አሰልጣኝ እንዳልካቸው ጫካ የዲላ ከተማ የወንዶች ቡድንን ከአንደኛ ሊግ ወደ ከፍተኛ ሊግ ካሳደጉ በኋላ በከፍተኛ ሊጉ የአንድ አመት ቆይታ አድርገው ወደ ሴቶቹ ቡድን ተመልሰዋል፡፡ አሰልጣኙ ስለ ዝግታቸው ለሶከር ኢትዮጵያ በሰጡት አስተያየት የተሸለ የውድድር ዘመን ለማሳለፍ እየተዘጋጁ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

“ዝግጅታችን ጥሩ ነው፡፡ ዘንድሮ በሁለተኛ አመታችን ላይ ነው ያለነው፡፡ ከጠንካራ ቡድኖች ጋር ስለምንጫወትም ተፎካካሪ ለመሆን አቅደናል፡፡ ከተቻለም ዋንጫውን ለማግኘት እንፋለማለን፡፡ ክለቡም ካለፈው የውድድር ዘመን ይልቅ ዘንድሮ የሚያደርግልን ድጋፍ ጨምሯል፡፡ ይህም መሻሻል ለሴቶች ትኩረት መሰጠቱን ያመላክታል፡፡›› ብለዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *