ጀማል ጣሰው ወደ ፋሲል አምርቷል

በዝውውር መስኮቱ በስፋት እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ፋሲል በሁሉም ስፍራዎች አዳዲስ ተጫዋቾች ለማስፈረም የቆረጠ ይመስላል።  ግብ ጠባቂው ጀማል ጣሰውም የቡድኑ 7ኛ አዲስ ተጫዋች መሆኑን ክለቡ ይፋ አድርጓል።

የውድድር ዘመኑን በድሬዳዋ ከተማ የሳምሶን አሰፋ ተጠባባቂ ሆኖ ያሳለፈው ጀማል ጣሰው ኮንትራቱ መጠናቀቁን ተከትሎ ወደ ድሬዳዋ ከተማ አምርቷል፡፡ የቀድሞው የኤሌክትሪክ ፣ ሀዋሳ ከተማ ፣ ደደቢት ፣ ኢት ቡና እና መከላከያ ግብ ጠባቂ በፋሲል ለመጀመርያ ተሰላፊነት በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ጥሩ ብቃት ካሳየው ሚኬል ሳማኬ ጋር መፎካከር ይጠበቅበታል።