የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ነገ የወዳጅነት ጨዋታ ያደርጋል

የሠላምና የወዳጅነት ውድድር መቅረቱን ተከትሎ የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ነገ በአዲስ አበባ ስታዲየም ጁቡቲን በወዳጅነት ጨዋታ የሚገጥም ይሆናል።

ከሚያዝያ 3 ጀምሮ በአስመራ ከተማ ይካሄዳል ተብሎ የታሰበው የሠላም እና የወዳጅነት ውድድር ላይ ለመሳተፍ ያለፉትን 15 ቀናት ዝግጅቱን ሲያደርግ የቆየው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የውድድሩ መቅረትን ተከትሎ ነገ ከጁቡቲ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ያደርጋል። የጁቡቲ ብሔራዊ ቡድን ትላንት አዲስ አበባ የገባ ሲሆን ዛሬም በአዲስ አበባ ስታዲየም እንደ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሁሉ የመጨረሻ ልምምዱን ሰርቷል።

ነገ 10:00 በአዲስ አበበ ስቴዲየም የሚካሄደው ይህ ጨዋታ ለተመልካች ክፍት እንደሆነ ፌዴሬሽኑ አሳውቋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

error: