ፌድሬሽኑ በድጋሚ ድሬዳዋ ከተማን አስጠንቅቋል

ፌድሬሽኑ ከወራት በፊት ሦስት ተጫዋቾችን ድሬዳዋ ከተማ ከህግ ውጪ አሰናብቷል በሚል ለተጫዋቾቹ የደመወዝ ክፍያን እንዲከፍል ቢወስንም ተግባራዊ አለማድረጉን በመግለፅ በድጋሚ ክለቡን አስጠንቅቋል፡፡

ድሬዳዋ ከተማ ዮናታን ከበደ፣ ኃይሌ እሸቱ እና ወሰኑ ማዜ ክለቡ ቀሪ የውል ኮንትራት እያለን ያለአግባብ አሰናብቶናል በሚል ለፌድሬሽኑ ክስ ማስገባታቸው ይታወሳል፡፡ ፌድሬሽኑ ጉዳዩን ሲመለከት ከቆየ በኃላ ደመወዛቸውን እንዲከፍል፤ በአስር ቀናት ውስጥም ተግባራዊ እንዲያደርግ ፌድሬሽኑ መወሰኑ ይታወሳል፡፡ ሆኖም ድሬዳዋ የፌዴሬሽኑ ወሳኔን በመቃወም ባለፈው ሳምንት መግለጫ የሰጠ ሲሆን ፌድሬሽኑ በድጋሚ ትላንት ውሳኔውን ተግባራዊ እንዲያደርግ አስጠንቅቋል።

ለሁለተኛ ጊዜ ለድሬዳዋ የተፃፈው ደብዳቤ ይህን ይመስላል፡-


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

error: