የፕሪምየር ሊግ አመራር ዐቢይ ኮሚቴ ነገ ስብሰባውን ያደርጋል

በቅርቡ ፕሪምየር ሊጉን ለመምራት በተመረጡ አባላት የተዋቀረው የፕሪምየር ሊግ ዐቢይ ኮሚቴ ከሰሞኑን ተዟዙረው ሲመለከቷቸው በነበሩ የክለቦችን የመጫወቻ ሜዳዎች ዙርያ እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት ያደርጋል፡፡

ነገ ረፋድ በፌዴሬሽኑ አዲሱ ህንፃ ላይ ለሁለተኛ ጊዜ በሚያካሂደው ስብሰባ ላይ በዋናነት በፕሪምየር ሊጉ ተካፋይ የሆኑ ክለቦች የሚያከናውኑባቸው ሜዳዎች ብቁነትን የሚገምግም ሲሆን በያዝነው ሳምንት ይህ ኮሚቴ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በቡድን በመሰማራት የሁሉንም የፕሪምየር ሊግ ክለቦች የመጫወቻ ሜዳዎች በመዟዟር ሲመለከት እንደነበረ ሶከር ኢትዮጵያ በአንድ አንድ ቦታዎች ተገኝታ ተመልክታለች።

ቡድኑ ባያቸው ጉድለቶች እና ክፍተቶች መሻሻል ያለባቸው እና በአፋጣኝ መስተካከል ስላለባቸው ሜዳዎችም ነገ በግልፅ ውይይት ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ነገ ይህ ስብሰባ ከሜዳ ግምገማነቱ በዘለለ ባለፈው ዓመት በነበሩ ክፍተቶች እና ዘንድሮ መሻሻል ስላለባቸው እንዲሁም ፕሪምየር ሊጉን በምን አይነት መንገድ እንምራው ስለሚሉ ጉዳዮች በዝርዝር ተመልክቶ ለክለቦች በፅሁፍ ተዘጋጅቶ በሰነድ መልክ እንደሚልክም ሰምተናል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ