ከፍተኛ ሊግ | ኢኮሥኮ ለፌዴሬሽኑ የቅሬታ ደብዳቤ አስገባ

በከፍተኛ ሊግ እየተሳለፈ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮፕሬሽን እግርኳስ ክለብ በፌዴሬሽኑ ላይ ጠንከር ያለ ተቃውሞ አቀረበ።

ባሳለፍነው ረቡዕ በጁፒተር ሆቴል የ2012 የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር የምድብ ድልድል በ27 ድጋፍ በ9 ተቃውሞ ይፋ መሆኑ ይታወቃል። በዕለቱም በኢኮስኮ በኩል በተደጋጋሚ የምድብ ድልድሉ ተገቢ አይደለም በማለት ተቋውሟውን እያነሱ እንደነበረ ታዝበናል።

ይህን ተከትሎ በትናንትናው ዕለት አራት ገፅ ያለው ዝርዝር ሀሳብ የያዘ ደብዳቤ ለፌዴሬሽኑ አስገብተዋል ” የምድብ ድልድሉ ፍፁም ኢ ፍትሐዊ በሆነ መንገድ የተዘጋጀ፣ ደንብን የጣሰ፣ የተወሰኑ ክለቦችን ለመጥቀምና ለመጉዳት፣ በግለሰቦች ፍቃድ ላይ ተመሠርቶ የተከናወነ ስለሆነ ከዚህ ደብዳቤ ጋር አባሪ በማድረግ ያቀረብነውን ዝርዝር መግለጫ ተመልክታቹሁ ህሊናችሁን በማያስቆጭ መልኩ ትክክለኛ ውሳኔ እንድትሰጡን በአክብሮት እንጠይቃለን።” ብለዋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ