ነገ የሚካሄደው የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ኮከቦች ምርጫ እጩዎች ታውቀዋል

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በ2011 ባካሄዳቸው 6 ሊጎች ላይ ጎልተው የወጡ ተጫዋቾች እና የተለያዩ የእግርኳስ ባለሙያዎችን ቅዳሜ ኅዳር 27 ቀን 2012 በካፒታል ሆቴል ከምሽቱ 12፡00 በሚደረግ ሥነ-ሥርዓት ለመሸለም ተዘጋጅቷል።

የሽልማቶቹ ዘርፍ ኮከብ አሠልጣኝ፣ ኮከብ ተጫዋች፣ ኮከብ ግብ አስቆጣሪ፣ ኮከብ ግብ ጠባቂ እንዲሁም ምስጉን ዋና ዳኛ እና ምስጉን ረዳት ዳኛ ሲሆኑ በተጨማሪም የሕይወት ዘመን ተሸላሚ እና ልዩ ተሸላሚዎችን ያካተተ ነው፡፡

ፌዴሬሽኑ ይፋ ያደረጋቸው ለኮከብ ተጫዋችነት እና ግብ ጠባቂነት በዕጩነት የያዛቸው የሚከተሉትን ይመስላሉ፡፡

ከአንደኛ ሊግ

ተጫዋችች

ፈቱ አብደላ – ከኮልፌ ቀራንዮ ክ/ ከተማ
በላይ ገዛኸኝ – ከባቱ ከተማ

ግብ ጠባቂዎች

ቴዎድሮስ ከለሎ – ከኮልፌ ቀራንዮ ክ/ ከተማ
ወንደሰን ረጋሳ – ከባቱ ከተማ

ከከፍተኛ ሊግ

ተጫዋቶች

ጌቱ ኃ/ማርያም – ከሰበታ ከተማ
አህመድ ሁሴን – ከወልቂጤ ከተማ
ሱራፌል ጌታቸው – ከሀዲያ ሆሳዕና

ግብ ጠባቂዎች

ሰለሞን ደምሴ – ከሰበታ ከተማ
ጆርጅ ደስታ – ከኢትዮጵያ መድን
አንተነህ ሀብቴ – ከገጣፎ ለገዳዲ

ከወንዶች ኘሪምየር ሊግ

ተጫዋቾች

ሱራፌል ዳኛቸው – ከፋሲል ከነማ
ሀብታሙ ገዛኸኝ – ከሲዳማ ቡና
አማኑኤል ገ/ሚካኤል – ከመቐለ 70 እንደርታ

ግብ ጠባቂዎች

ፍሊፕ ኦቮኖ – ከመቐለ 70 እንደርታ
ሳማኬ ሚኬል – ከፋሲል ከነማ
መሳይ አያኖ – ከሲዳማ ቡና

ከሴቶች ኘሪምየር ሊግ 1ኛ ዲቪዚዮን

ተጫዋቾች

ሰናይት ቦጋለ – ከአዳማ ከተማ
ሴናፍ ዋቁማ – ከአዳማ ከተማ
ምርቃት ዘለቀ – ከሀዋሳ ከተማ

ግብ ጠባቂዎች

ማርታ በቀለ – ከመከላከያ
ንግስት መአዛ – ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
እምወድሽ ይርጋሸዋ – ከአዳማ ከተማ እ

ከሴቶች ፕሪምየር ሊግ 2ኛ ዲቪዚዮን

ተጫዋቾች

ዮርዳኖስ በርኸ – ከመቐለ 70 እንደርታ
ንግስት ኃይሉ – ከአቃቂ ክ/ከተማ
ቤተልሔም አምሳሉ – ከፋሲል ከነማ

ግብ ጠባቂዎች

አዲስ አብርሃም – ከአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ
አይናለም ሽታ – ከቂርቆስ ክ/ከተማ
ጽዮን ተፈራ – ከሻሸመኔ ከተማ


© ሶከር ኢትዮጵያ