ሙጂብ ቃሲም ለቀናት ከልምምድ ይርቃል

በዋልያዎቹ ስብስብ ውስጥ ተካቶ በዝግጅት ላይ የሚገኘው አጥቂው ሙጂብ ቃሲም ጉዳት አስተናግዷል።

ውስብስብ ችግሮችን እያጋጠሙት የሚገኘው በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከአስራ አምስት ቀን በኃላ ወሳኝ አፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታ ከኒጀር ጋር ይጠብቀዋል። ለዚህም እንዲረዳው ቅድመ ዝግጅቱን መስከረም ወር መጨረሻ ጀምሮ ሁለት ያቋም መፈተሻ ጨዋታም ማድረጉ ይታወቃል። 26 ተጫዋች በመያዝ ጠንከር ያለ ዝግጅቱን እያደረገ ከሚገኙ የቡድኑ ስብስብ መካከል በዛሬው ዕለት አጥቂው ሙጂብ ቃሲም ጉዳት አጋጥሞታል። የጉዳቱ መጠን ምን ያህል እንደሆነ እና ከልምምድ ለምን ያህል ጊዜ እንደሚያርቀው ሙጂብን ጠይቀነው ተከታዩን አጭር ምላሽ ሰጥቶናል።

“የገጠመኝ ጉዳት የቀኝ ታፋዬን ነው ያመመኝ። ልምምዱን መቀጠል ስላልቻልኩ አቋርጬ ወጥቻለው። የህክምናው ባለሙያው ለሁለት ቀን እረፍት አድርግበት የሚያሰጋ ነገር የለውም ብሎ ነግሮኛል። ሁለት ቀን እረፍት አድርጌ በቀጣይ ወደ ልምምድ እመለሳለው ብዬ ተስፋ አደርጋለው።”

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!