“አቡበከር ናስር ለማሜሎዲ ሰንዳውንስ ፊርማውን አኑሯል” መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]

የኢትዮጵያ ቡናው አጥቂ አቡበከር ናስር ከደቡብ አፍሪካው ክለብ ማሜሎዲ ሰንዳውንስ ጋር ያለው ጉዳይ መጨረሻ ማግኘቱን መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ ይፋ አድርገዋል።

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የአንድ የውድድር ዘመን ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ተጫዋች የሆነው አቡበከር ናስር ከበርካታ ክለቦች የእናስፈርምህ ጥያቄ እየቀረበለት እንደነበር ይታወቃል። የደቡብ አፍሪካው ሀያል ክለብ ማሜሎዲ ሰንዳውንስም ተጫዋቹን የግሉ ለማድረግ ከቀናት በፊት የሙከራ ጊዜ ሰጥቶት እንደነበር መዘገቡ ይታወሳል። በአሁኑ ሰዓት የድሬዳዋ ከተማ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተሳታፊ ክለቦችን እና ባለድርሻ አካላትን እንኳን ደህና መጣችሁ ለማለት ባዘጋጀው መርሐ-ግብር ላይ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር የቦርድ ሰብሳቢ መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ ስለ አቡበከር ናስር አዲስ መረጃ ይፋ አድርገዋል።

“አቡበከር ናስር ዛሬ ከደቡብ አፍሪካው ክለብ ማሜሎዲ ሰንዳውንስ ጋር ውል ተፈራርሟል። ተጫዋቹ ከ4 ወር በኋላ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሲያልቅ ወደ ጆሀንስበርግ ይሄዳል። የማሜሎዲ ሳንዳውንስ ተጫዋችም ይሆናል። ግን አሁን በውሰት ኢትዮጵያ ቡና ተመልሶ ዓመቱን ይጨርሳል።

“በርካታ ክለቦች የአፍሪካ ዋንጫው ላይ ተገኝተን እናስፈርመዋለን ብለው ነበር። ግን ተጫዋቹ አጥቂ ቦታ ላይ አልተጫወተም። አቡበከር ነው የሚሻለው ጌታነህ? እኛ አሠልጣኝ ባንሆንም ከ50 ዓመት በላይ የኢትዮጵያን እግርኳስ ተመልክተናል። የሆነው ሆኖ ተጫዋቹ ከሳንዳውንስ ጋር ዛሬ ተፈራርሟል።”