👉 “አንድ አንድ በሬ ወለድ የሆኑ ሀሳቦች ትክክል አይደሉም።” አቶ ባሕሩ ጥላሁን

👉 “አንድ አንድ በሬ ወለድ የሆኑ ሀሳቦች ትክክል አይደሉም።” አቶ ባሕሩ ጥላሁን

👉 “አንድ አንድ በሬ ወለድ የሆኑ ሀሳቦች ትክክል አይደሉም።

👉 “ሱራፌልን በተመለከተ ፍፁም ሐሰት ነው።”

👉 “በክፉኛ ልባዊ ቅናት የተነሳ የሚዘወሩ ሀሳቦች ናቸው።”

ሱራፌል ዳኛቸው ስላለበት ሁኔታ እና ፌዴሬሽኑ ከሚዲያ ጋር ስላለው ግንኙነት አስመልክቶ ፌዴሬሽኑ ግልፅ አቋሙን አሳውቋል።

ጋዜጣዊ መግለጫው እንደቀጠለ ነው። የሚዲያ ባለሚያዎችም ጥያቄዎችን ማንሳታቸው ቀጥለዋል። ሱራፌል ዳኛቸው በሙከራ ከሄደ በኋላ የመጫወት ዕድል አላገኘም? የመኖርያ ፍቃድ የለውም? የወዳጅነት ጨዋታ ብቻ አድርጓል ይህ ሱራፌል ላይ የደረሰው ነገር ሌሎቹ አራቱ ለሙከራ በአሜሪካ የቀሩት ተጫዋቾች ላይ ላለመድረሱ ምንድነው ማረጋገጫው በሚል  አቶ ባህሩ ጥላሁን ያለውን ሁኔታ ጠንከር ባለ ሁኔታ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

“ሱራፌል ዳኛቸውን በተለከተ የስራ ፍቃድ የለውም የተባለው ሐሰት ነው። ሱራፌል የስራ ፍቃድ አለው ለቡድኑ ጨዋታዎችን አድርጎ ያውቃል። አሁን ላይ ያለበት ሁኔታ ጉዳት ላይ ነው። በጉዳት ምክንያትም ብሔራዊ ቡድኑን መቀላቀል አልቻለም። አንድ አንድ በሬ ወለድ የሆኑ ሀሳቦች ትክክል አይደሉም። ምክንያቱም ሱራፌል የስራ ፍቃድ ያለው እና ለቡድኑም እየተጫወተ ስለሆነ። እንደጠበቅነው ሱራፌል አቋሙን ማሳየት አልቻለም በተደጋጋሚ እያሳየን አይደለም ከተባለ በእግርኳሰ ህይወት ውስጥ የከፍታ፣ የዝቅታ ጊዜ ሊኖር ይችላል። ይህን ለማሸነፍ ጠንክሮ እየሰራ ነው። ከዚህ ውጭ በተደጋጋሚ የስራ ፍቃድ የለውም የሚባለው እኛ ማብራሪያ ከዚህ ቀድም ሰጥተናል ልጁንም ማናገር ይቻላል። ካሉ በኋላ ፌዴሬሽኑ ከሚዲያ ጋር ስላለው ግንኙነት አስመልክቶ አቶ ባሄሩ ሲናገሩ

“ብሔራዊ ቡድን በተመለከተ ሁላችንም ያለን አንድ ሀገር ነው የሚሰጡት አስተያየቶች አስተማሪ በሆነ መልኩ ለትውልድ ቀሪ ሆነው የሚቀመጡ መሆን ታዳጊውንም፣ በእውቀት የሚከታተለውን በብቃት እንዲያዳምጠው የሚሆን አስተያየት መስጠት አለበት። ከሙያው ባፈነገጠ መልኩ የሚሰጥ እና ለቃላት አጠቃቀሜ ይቅርታ ክፉኛ ልባዊ ቅናት የተነሳ የሚዘወሩ ሀሳቦች ናቸው። ስለዚህ እነዚህ ነገሮች ሊስተካከሉ ይገባል። ብሔራዊ  ቡድን ተጫዋቾች ናቸው የሚሰጡት ሀሳቦች የምንገልፅባቸው መንገዶች ሊስተካከሉ ይገባል። የሚሰጡት ሀሳቦች ስሜታዊ ሳይሆን ሀሳቦችን ማስቀመጥ ያስፈልጋል።
ብለዋል።”

አያይዘውም የብሔራዊ ቡድኑ ተጫዋቾች ለእያንዳንዳቸው  ለአበል እና ያሸነፉበት ከአቶ ጆን ማሞ አንድ ሺህ ጨዋታውን ላሸነፉበት እንዲሁም ሰባት መቶ አበል በጥቅሉ አንድ ሺህ ሰባት መቶ ዶላር ለቡድኑ እንደተሰጣቸው ገልፀዋል።