ድሬዳዋ ከተማ የመጀመሪያ ተጫዋቹን አስፈረመ

ድሬዳዋ ከተማ የመጀመሪያ ተጫዋቹን አስፈረመ

በአሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለ የሚመሩት ብርቱካናማዎቹ ተከላካይ አስፈርመዋል።

በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን በአሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለ መሪነት ዓመቱን ያጠናቀቀው ድሬዳዋ ከተማ በሊጉ ለመቆየት ሲያደርግ የነበረውን ጥረት በመጨረሻዎቹ ሳምንታት ላይ ማሳካት የቻለ ሲሆን ለቀጣዩ የውድድር ዘመንም ቡድኑ ራሱን ለማጠናከር ይረዳው ዘንድ የክረምቱ የመጀመሪያ ፈራሚውን በእጁ አስገብቷል።

ቡድኑን የተቀላቀለው የመሐል ተከላካዩ ሬድዋን ሸረፋ ነው። የቀድሞው የበደሌ ከተማ ተከላካይ ከጅማ አባጅፋር ጋር ከነበረው ቆይታ በኋላ በአዳማ ካሳለፈው የሁለት ዓመታት ቆይታ የነበረው ሲሆን ዘንድሮ በሊጉ ጥሩ ጊዜ በማሳለፍ ለቀጣይ ሁለት ዓመታት ማረፊያውን የቀድሞው አሰልጣኙ ይታገሱ እንዳለው ድሬዳዋ አድርጓል።