ኢትዮ ኤሌክትሪክ የሁለት ተጫዋቾች ውል አራዘመ

ኢትዮ ኤሌክትሪክ የሁለት ተጫዋቾች ውል አራዘመ

በአሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ የሚመራው ኤሌክትሪክ የነባር ተጫዋቾች ውል አራዝሟል።

በ2017 የውድድር ዓመት በ47 ነጥብ 9ኛ ደረጃን ይዘው ያጠናቀቁት ኢትዮ ኤሌክትሪኮች ለቀጣይ የውድድር ዓመት ራሳቸውን ለማጠናከር የሁለት ነባር ተጫዋቾችን ውል በማራዘም ወደ ዝውውር መስኮቱ ገብተዋል።

በቡድኑ ለተጨማሪ ዓመት ለመቆየት የተስማሙት ደግሞ ባለፈው የውድድር ዓመት ሀምበሪቾን በመልቀቅ በተጠናቀቀው ዓመት ኢትዮ ኤሌትሪክን በመቀላቀል በአመዛኙ ጨዋታዎች ላይ ተሳትፎ ያደረገው አማካይ በፍቃዱ አስሳኸኝ እንዲሁም ባለፉት ዓመታት በሻሸመኔ ከተማ ቆይታ ካደረገ በኋላ በ2017 የውድድር ዓመት በኤሌክትሪክ መለያ በ31 ጨዋታዎች ተሳትፎ በማድረግ በመስመር አጥቂነት እና በመስመር ተከላካይነት 1729 ደቂቃዎች ቡድኑን ያገለገለው አሸናፊ ጥሩነህ ናቸው።

አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ በመቀጠል የዕቅዳቸው አካል የሚሆኑ ሌሎች ተጫዋቾችን በማስፈረም እንደሚቀሳቀሱ ይጠበቃል።