የነባር ተጫዋቾቹን ውል በማራዘም ተጠምደው የሚገኙት ቻምፒዮኖቹ የግራ መስመር ተከለካያቸውን ለማቆየት ተስማምተዋል።
በአሰልጣኝ ገብረመድን ኃይሌ እየተመሩ የ2017 የሊጉ አሸናፊ ሆነው ያጠናቀቁት ኢትዮጵያ መድኖች ከዚህ ቀድም የግብዘቡን አቡበከር ኑራ፣ የበረከት ካሌብ እና የንጋቱ ገብረስላሴን፣ መሐመድ አበራ እና ረመዳን የሱፍን ውል እንደማራዘማቸው ሁሉ አሁን ደግሞ የወጣቱን ግራ መስመር ተከላካይ ያሬድ ካሳይን ለተጨማሪ ዓመት ለማቆየት መስማማታቸውን አውቀናል።
ወጣቱ የግራ መስመር ተከላካይ ያሬድ ካሳይ ከታዳጊ ቡድን እስከ ዋናው ቡድን ድረስ የሌላ ክለብ ማልያ ሳያደርግ ዕድገቱን ጠብቆ እያገለገለ ሲሆን ዘንድሮም ቡድኑ ባደረጋቸው 29 ጨዋታዎች ላይ ተሳትፎ በማድረግ በተለይ መከላከል ቀዳሚው ስረሰ አድርጉ የቡድኑን የማጥቃት አቅም በማሳደግ ክለቡ የሊጉን ዋንጫ እንዲያነሳ በማስቻል ረገድ ስኬታማ ቆይታ አድርጓል። ያሬድ በአሳዳጊው ቤት ለአንድ ዓመት ለመቆየት እንደተስማማም አውቀናል።