መቻል ወደ ዝውውሩ ገብቷል

መቻል ወደ ዝውውሩ ገብቷል

መቻሎች አንድ አማካይ ለማስፈረም በመስማማት ወደ ዝውውሩ መግባታቸው ታውቋል።

አሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረትን ለአንድ ዓመት በማስፈረም ለቀጣይ ዓመት ውድደር መዘጋጀት የጀመሩት መቻሎች አሁን ደግሞ የመጀመርያ ፈራሚያቸው ለማግኘት መስማማታቸውን ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ያመላክታል።

ቡድኑን ለመቀላቀል የተስማማው አማካዩ ብሩክ ማርቆስ መሆኑ ታውቋል። ከሀድያ ሆሳዕና የውስጥ ውድደር ባሳየው ድንቅ እንቅስቃሴ በቀጥታ ወደ ዋናው ቡድን በመቀላቀል ያለፉትን አራት ዓመታትን ጥር አገልግሎት በመስጠት ሲጫወት የቆየው አማካዩ አሁን ሁለተኛ ክለቡ በመሆን ለመቻል ለሁለት ዓመት ለመጫወት መስማማቱ ታውቋል።