ኢትዮጵያ ቡና ምክትል አሰልጣኝ ሾመ

ኢትዮጵያ ቡና ምክትል አሰልጣኝ ሾመ

የአሰልጣኞች ቡድኑን በአዲስ መልክ እያዋቀረ የሚገኘው ኢትዮጵያ ቡና የቀድሞ ተጫዋቹን በረዳት አሰልጣኝነት መሾሙን ይፋ አድርጓል።


የዐቢይ ካሣሁን ምክትል በመሆን የተሾመው ኃይሉ አድማሱ “ቻይና” ነው። የቀድሞው የኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ኢትዮጵያ ቡና ድንቅ አማካይ ወደ አሰልጣኝነት ከተሸጋገረ በኋላ በኢትዮ ኤሌክትሪክ ወጣት ቡድን እንዲሁም ዋናው ቡድን በምክትል አሰልጣኝነት ማገልገል የቻል ሲሆን በአንድ ዓመት ውል ቡናን መቀላቀሉን ክለቡ አስታውቋል።