ኢትዮጵያ መድን የመስመር አጥቂ አስፈርሟል

ኢትዮጵያ መድን የመስመር አጥቂ አስፈርሟል

በአሰልጣኝ ገብረመድን ኃይሌ የሚሰለጥኑት ሻምፒዮኖቹ የመጀመርያ ፈራሚያቸውን አግኝተዋል።

የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸው የጀመሩት መድኖች ውላቸው የተጠናቀቁ ወሳኝ ተጫዋቾቻውን የግብ ዘቡን አቡበከር ኑራ ፣ ንጋቱ ገብረሥላሴ፣ ያሬድ ካሳይ እና ረመዳን የሱፍን ውል ማራዘማቸው ሲታወስ አሁን ደግሞ ፊታቸውን አዳዲስ ተጫዋቾች ወደ ማስፈረም በመግባት የመጀመርያ ፈራሚያቸውን አግኝተዋል።

ለሻምፒዮኖቹ ለመጫወት የተስማማው የመስመር አጥቂው ብሩክ ሙልጌታ ነው። ከዚህ ቀደም በከፍተኛ ሊግ በኮልፌ ቀራንዮ፣ ሲዳማ ቡና እንዲሁም ኢትዮጵያ መድን ድርጅት እና መቐለ 70 እንደርታ ቆይታ የነበረው ተጫዋቹ ከአንድ ዓመት የመቐለ ቆይታ በኋላ ወደ ቀድሞ ቤቱ ተመልሷል።