ነብሮቹ ሁለት ተጫዋች አስፈርመዋል

ነብሮቹ ሁለት ተጫዋች አስፈርመዋል

ሀድያ ሆሳዕና ሁለት አማካይ ተጫዋች ሲያስፈርሙ የአንድ ነባር ተጫዋችን ውል አራዝመዋል።

አሰልጣኝ ካሊድ መሐመድን የሚሰለጥኑን ሀድያ ሆሳዕናዎች አሸናፊ ኤልያስን በማስፈረም ወደ ዝውውሩ የገቡ ሲሆን አሁን ደግሞ ሁለት ተጫዋቾችን በማስፈረም የአንድ የነባር ተጫዋቻቸውን ውል ማደሳቸው ታውቋል።

የመጀመርያ ፈራሚው አማካይ ሙሴ ከበላ ነው። በአስኮ ፕሮጀክት የእግርኳስ ህይወቱን የጀመረው ሙሴ በመቀጠል በኢትዮጵያ ቡና ከታዳጊ እስከ ዋናው ቡድን በኋላም በጅማ አባ ጅፋር ፣ ኢትዮ ኤሌትሪክ ያለፉትን አንድ ዓመታት በአዳማ ከተማ በነበረው ቆይታ በ31 ጨዋታዎች 2539 ቡድን ያገለገለው ሙሴ አሁን ለሁለት ዓመት መዳረሻው ሀድያ ሆሳዕና ሆኗል።

ሌላኛው ቡድኑን ለመቀላቀል የተስማማው መስመር ተጫዋቹ ኤልያስ አሕመድ ነው። ባለፈው የውድድር ዓመት ከብርቱካናማዎቹ ጋር በነበረው ቆይታ በሀያ አምስት ጨዋታዎች ተሰልፎ 1754 ደቂቃዎች ቡድኑን ያገለገለው የመስመር ተጫዋቹ ኤልያስ አሕመድ ላለፉት ቀናት ከቡድኑ ጋር ያደረገው ድርድር በስምምነት መገባደዱን ተከትሎ በቀጣይ ቀናት በይፋ ቡድኑን ይቀላቀላል ተብሎ ይጠበቃል ። ከዚ ቀደም በልደታ ኒያላ፣ ሐረር ሲቲ፣ ሰበታ ከተማ፣ ከ2011 ጀምሮ ደግሞ በፕሪምየር ሊግ ተሳታፊ ለሆኑት ባህርዳር ከተማ፣ ጅማ አባጅፋር፣ አዳማ ከተማና ድሬዳዋ ከተማ መጫወት የቻለው ተጫዋቹ የቡድኑ ስድስተኛ ፈራሚ ለመሆን ተቃርቧል።

ውሉን ያራዘመው ግብ ጠባቂው ያሬድ በቀለ ነው ከሀድያ ከተማ ታዳጊ ቡድን ጀምሮ ያለፉትን ሦስት ዓመት በዋናው ቡድን ቆይታ  ያደረገው ወጣቱ ግብጠባቂ ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት በቡድኑ ለመቆየት ውሉን አድሷል።