ስድስት ተጫዋቾች ብሔራዊ ቡድኑን አልተቀላቀሉም

ስድስት ተጫዋቾች ብሔራዊ ቡድኑን አልተቀላቀሉም

ዋልያዎቹ ከግብፅ እና ሴራሊዮን ጋር ለሚያከናውኗቸው የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ዝግጅት ቢጀምሩም ስድስት ተጫዋቾች ቡድኑን አልተቀላቀሉም።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከግብፅ እና ሴራሊዮን ጋር ለሚያከናውናቸው የዓለም ዋንጫ ማጣርያ 7ኛ እና 8ኛ ጨዋታዎች ዝግጅት አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ጥሪ ያደረጉላቸው ተጫዋቾች ትናንት ወደ ሆቴል ገብተው ዛሬ ልምምድ ሲጀምሩ ስድስት ተጫዋቾች በልምምዱ ላይ እንዳልተገኙ ሶከር ኢትዮጵያ በስፍራው ተገኝታ አረጋግጣለች።

አራቱ በአሜሪካ የሙከራ ጊዜ ላይ የነበሩት ማለትም ከነዓን ማርክነህ ፣ ቢኒያም በላይ ፣ ሀብታሙ ተከሰተ እና ራምኬል ጀምስ ዛሬ ወደ ሀገር ቤት በመግባታቸው ለልምምዱ አለመድረሳቸው ሲታወቅ ዛሬ ቡድኑን ተቀላቅለው ነገ ልምምድ ይጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ሌሎቹ ሁለቱ ተጫዋቾች ደግሞ ረመዳን የሱፍ እና ሱሌይማን ሀሚድ ሲሆኑ ተጫዋቾቹ የፓስፖርት ጊዜያቸው በማለቁ እሱን ለማስተካከል እያደረጉት ባለው ጥረት ምክንያት አለመገኘታቸውን አረጋግጠናል።