ለ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አዲስ አሰልጣኝ ተሹሟል

ለ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አዲስ አሰልጣኝ ተሹሟል

በፖላንድ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የ2026 የሴቶች ከ20 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ ለማለፍ የማጣሪያ ጨዋታ የሚጠብቃቸው የትናንሾቹ ሉሲዎች አለቃ ይፋ ሆኗል።

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በፖላንድ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የ2026 የሴቶች ከ20 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ ለማለፍ የማጣርያ ውድድሩን መስከረም ወር ላይ ይጀምራል።

ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድኑ በሁለተኛ ዙር ማጣርያ መስከረም 11 እና 18 የሚያከናውን ሲሆን የቦሌ ክ/ከተማ የሴቶች ቡድን አሰልጣኝ የሆነው ቻለው ለሜቻ የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ በመሆን መሾሙን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ይፋ አድርጓል።

* አሰልጣኙ በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ላለፉት ስምንት ዓመታት ብዙ ታዳጊዎችን በማሰልጠን ወደ ትልቅ ደረጃ እንዳሳደገ ይታወቃል።