ያለፈውን አንድ ዓመት በኢትዮ ኤሌክትሪክ ቆይታ የነበረው የመስመር አጥቂ ውሉን ማራዘሙን አውቀናል።
እምብዛም ወደ ዝውውሩ በስፋት ያልገባው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከዚህ በፊት የሰባት ተጫዋቾችን ውል በማራዘም እና ተከላካዩ በረከት ወልደዮሐንስን አዲስ ፈራሚ ማድረጉ ይታወቃል። አሁን ደግሞ የመስመር አጥቂያቸውን እዮብ ገብረማርያምን ለተጨማሪ ዓመት ለማቆየት መስማማታቸውን ሰምተናል።
ባሳለፍነው የውድድር ዘመን በኢትዮ ኤሌክትሪክ መለያ 30 ጨዋታዎች ላይ በመሰለፍ 1765 ደቂቃዎች ቡድኑ ያገለገለ ሲሆን በስሙ የተመዘገቡ አራት ጎሎችን አስቆጥሮ ነበር። ከዚህ ቀደም በኢትዮ መድን፣ በሻሸመኔ ከተማ ተጫውቶ ያሳለፈ እዮብ በድጋሚ በኢትዮ ኤሌክትሪክ ቤት ለመቆየት ተስማምቷል።