ዩጋንዳዊው አጥቂ በቻምፒዮኖቹ ቤት ይቆያል

ዩጋንዳዊው አጥቂ በቻምፒዮኖቹ ቤት ይቆያል

ወደ ሀገራችን ከመጣ ወዲህ ጥሩ የውድድር ጊዜን እያሳለፈ የሚገኘው ዩጋንዳዊው አጥቂ ውሉን አራዝሟል።

ከአንድ ዓመት ከስድስት ወር በፊት በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በሻሸመኔ ከተማ መለያ እራሱን በሊጉ ያስተዋወቀው የዩጋንዳ ዜግነት ያለው አለን ካይዋ በያዝነው ዓመት ነበር መድኖችን በመቀላቀል ስኬታማ ቆይታ ያደረገው። አሁን በድጋሚ በቻምፒዮኖቹ ቤት ለተጨማሪ ዓመት ለመቆየት መስማማቱን አውቀናል።

በዚህ ዓመት 22 ጨዋታዎች ተሳትፎ 1258 ደቂቃዎች ቡድኑን በማገልገል አምስት ጎሎችን በማስቆጠር ክለቡ የሊጉን ዋንጫ እንዲያነሳ ካደረጉ ተጫዋቾች አንዱ ሲሆን ወደ ሀገር ቤት ከመምጣቱ አስቀድሞ የእግርኳስ ሕይወቱን በሀገሩ ክለቦች ሶዋና ፣ ቫይፐርስ እና ኤክስፕረስ በተባሉ ቡድኖች ቆይታ አድርጎ ነበር።