ስሑል ሽረ የስያሜ ለውጥ አድርጓል

ስሑል ሽረ የስያሜ ለውጥ አድርጓል

ከዚህ ቀደም “ስሑል ሽረ እግርኳስ ክለብ” በሚል ስያሜ ይታወቅ የነበረው ክለብ ከዚህ በኋላ በሌላ ስያሜ እንደሚጠራ ለሶከር ኢትዮጵያ አሳውቋል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን የብሔር እና ሃይማኖታዊ ይዘት ያላቸው ስያሜዎችን የሚጠቀሙ ክለቦች ስያሜያቸውን እንዲያስተካክሉ ባወጣው መመሪያ መሠረት ስሑል ሽረ ቀዳሚው ማስተካከያ ያደረገው ክለብ ሆነዋል።

በዚህም መሠረት ከዚህ ቀደም “ስሑል ሽረ እግርኳስ ክለብ” በሚል ይጠቀምበት የነበረውን መጠርያ ወደ “ሽረ ምድረገነት እግር ኳስ ክለብ” ስለመለወጡ ክለቡ ለሶከር ኢትዮጵያ በላከው መረጃ አሳውቋል።

በቀጣይ ሌሎች ክለቦችም ማስተካከያ ያደርጋሉ ተብሎም እንደሚጠበቅ ቢገመትም ፌዴሬሽኑ እንደቀዚህ ቀደሙ የአቋም መለሳለስ ያሳያል ወይስ በአቋሙ ፀንቶ መመርያውን ያስተገብራል የሚለው ተጠባቂ ነው።

የ “ሽረ ምድረ ገነት እግርኳስ ክለብ” ዓርማ ይህንን ይመስላል 👇