ሽረ ምድረገነት አማካዩን አስፈረመ

ሽረ ምድረገነት አማካዩን አስፈረመ

ባለፉት ዓመታት በመቻል ቆይታ የነበረው አማካይ ወደ ሽረ ምድረ ገነት አመራ።

አሰልጣኝ ዳኒኤል ፀሐዬን በዋና አሰልጣኝነት በመቅጠር ለቀጣይ ውድድር ዓመት ቡድናቸውን ለማጠናከር በእንቅስቃሴ ላይ ያሉት እና ቀደም ብለው መክብብ ደገፉ እና ተካልኝ ደጀኔን ያስፈረሙት ሽረ ምድረገነቶች አሁን ደግሞ የክረምቱ የዝውውር መስኮት ሦስተኛ ፈራሚያቸውን አግኝተዋል። ወደ ቡድኑ ለማምራት የተስማማው ደግሞ አማካዩ በኃይሉ ግርማ ነው። በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በ28 ጨዋታዎች ተሳትፎ 1947′ ደቂቃዎች ቡድኑን ያገለገለው ተጫዋቹ ከጦሩ ጋር የነበረውን ውል መጠናቀቁን ተከትሎ ከረዥም ዓመታት ቆይታ በኋላ ከቡድኑ ጋር ተለያይቶ ወደ ሽረ ምድረ ገነት ፌርማውን አኑሯል።

ከሙገር ሲሚንቶ በኋላ ወደ መቻል አምርቶ በቡድኑ የሦስት ዓመታት ቆይታ ካደረገ በኋላ አንድ የውድድር ዓመት በሰበታ ከተማ ተጫውቶ ዳግም ወደ መቻል በማምራት ያለፉትን አራት ዓመታት በቡድኑ ቆይታ የነበረው ተጫዋቹ አሁን ደግሞ በሁለት አጋጣሚዎች ሰባት ዓመታትን ያገለገለበትን ቡድን በመልቀቅ ወደ ሽረ ምድረገነት ተቀላቅሏል።