የመስመር አጥቂው ውሉን አራዝሟል

የመስመር አጥቂው ውሉን አራዝሟል

ከአንድ ክለብ ውጭ ሌላ መለያ ለብሶ የማያቀው የመስመር አጥቂው በአሳዳጊው ክለብ የሚያቆየውን ውሉን አራዝሟል።

በአሰልጣኝ ስዩም ከበደ የሚመሩት አዳማ ከተማዎች ከትናንት በስቲያ ዝግጅታቸውን በመቀመጫ ከተማቸው ጀምረዋል። ጠንካራ ዝውውሮችን በመፈፀም ቡድናቸውን ያጠናከሩት አዳማዎች አሁን ደግሞ የመስመር አጥቂውን ቢንያም ዐይተን ውል አራዝመዋል።

በ2013 አጋማሽ ላይ ወደ ዋናው ቡድን በማደግ ለአዳማ ከተማ መጫወት የቻለው ቢኒያም ያለፉትን አራት ዓመት ከመንፈቅ ቡድኑን በጥሩ ሁኔታ እያገለገለ ቆይቷል። ከአዳማ ተስፋ ቡድን የተገኘው ቢኒያም 2016 የወጣት ተስፈኛ ኮከብ ተጫዋች ሽልማት ያገኘ ሲሆን ምንም እንኳን ለአንድ ዓመት ቀሪ ኮንትራት ቢኖረውም ተጨማሪ አንድ ዓመት በመጨመር በአሳዳጊ ክለቡ የሚያቆየውን ውል አሻሽሏል።