ባህር ዳር ከተማ ወሳኝ ዝውውር ፈፅሟል

ባህር ዳር ከተማ ወሳኝ ዝውውር ፈፅሟል

በአሠልጣኝ ደግአረገ ይግዛው የሚመራው ባህር ዳር ከተማ አጥቂ አስፈርሟል።

የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን በአዳማ እየከወኑ የሚገኙት ባህር ዳር ከተማዎች በአብዛኛው ወጣት ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸው በማምጣት ቡድናቸውን እያዋቀሩ እንደሚገኙ ይታወቃል። በዛሬው ዕለት ደግሞ የመስመር አጥቂው አማኑኤል ገብረሚካኤልን ማስፈረማቸውን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።

የቀድሞ የመቐለ 70 እንደርታ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋች የነበረው አማኑኤል ያለፉትን ሁለት ዓመታት በፋሲል ከነማ ቤት ግልጋሎት የሰጠ ሲሆን አሁን መዳረሻው የዐፄዎቹ ጎረቤት የሆኑት የጣናው ሞገዶቹ ቤት ሆኗል።