ሲዳማ ቡና ሁለገቡን ተጫዋች አሰፈርሟል

ሲዳማ ቡና ሁለገቡን ተጫዋች አሰፈርሟል

ቡድኑን በማጠናከር ላይ የሚገኘው ሲዳማ ቡና የኢኳቶሪያል ጊኒ ዜግነት ያለው ተጫዋች አስፈርሟል።

ቡድናቸውን በማጠናከር ላይ የሚገኙት ሲዳማ ቡናዎች ከደቂቃዎች በፊት ካሜሮናዊ አጥቂ እንዳስፈረሙ የነገርናችሁ ሲሆን አሁን ደግሞ የኢኳቶሪያል ጊኒ ዜግነት ያለው የመስመር አጥቂ ማስፈረማቸውን አረጋግጠናል።


ቡድኑን የተቀላቀለው ተጫዋች ፌዴሪኮ ንሱ ንጉኤማ ሲሆን በሀገሩ ክለብ ካኖ ስፖርት የእግርኳስ ጅማሮውን በማድረግ ወደ ሞልዶቫ አቅንቶ ለዳይናሞ አውቶ ቲራስፖል እና ለኤፍሲ ባልቲ ከተጫወተ በኋላ ባለፈው ዓመት ወደ ሀገሩ ተመልሶ ለቀድሞ ክለቡ ካኖ ስፖርት ተጫውቷል። 1 ሜትር ከ 65 ሴንቲ ሜትር የሚረዝመው ተጫዋች በዋነኝነት በቀኝ መስመር አጥቂ አማካይ ስፍራ ላይ ይጫወታል።

ለብሔራዊ ቡድኑ በአራት ጨዋታዎች ግልጋሎት የሰጠው ተጫዋቹ ማረፊያውን የኢትዮጵያው ክለብ ሲዳማ ቡና አድርጓል።