“ኑናራ ዲያጌ ኡባ ጦንያጋ” አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ

“ኑናራ ዲያጌ ኡባ ጦንያጋ” አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ

👉 “ኑናራ ዲያጌ ኡባ ጦንያጋ” አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ

የቀድሞ የዋልያዎቹ አለቃ በብሔራዊ ቡድን ስለነበራቸው ቆይታ እና አሁን ስለተረከቡት ኃላፊነት ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር አጭር ቆይታ አድርገዋል።

ከሰዓታት በፊት የወላይታ ድቻ ክለብ የቦርድ አመራሮች ሰፊ ስብሰባ ካደረጉ በኋላ ቡድኑ በዋና አሰልጣኝነት እንዲረከቡ የቀድሞ ታሪካዊ አሰልጣኛቸውን ዳግም ለመቅጠር መስማማታቸውን አስነብበናችሁ ነበር። ሶከር ኢትዮጵያ አሰልጣኝ መሳይ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ስለበራቸው ቆይታ እና አሁን ስለተረከቡት ኃላፊነት አስመልክቶ ከዝግጅት ክፍላችን ጋር አጭር ቆይታ አድርገዋል እንዲህ አድርገን አቅርበነዋል።

ስለ ብሔራዊ ቡድን ቆይታቸው

“በመጀመርያ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ። ይህን ዕድል የሰጡኝን አሰልጣኝ ገብረመድኅን ፣ ዶ/ር ዳኛቸው እንዲሁም የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት እና ዋና ሥራ አስፈፃሚውን አምነውብኝ ለእኔ ይህን ትልቅ ኃላፊነት ስለሰጡኝ ፣ በነበርኩበት ጊዜ ስለተባበሩኝ አመሰግናለሁ። በቆይታዬም የምችለውን ለሀገር ለመስራት ጥረት አድርጌአለሁ። እንደዚሁም የደረጃ ለውጥ ነበር። በተሰጠኝ ከሜዳ ውጭ አራት ጨዋታ አሸንፈናል። ይህ ቀላል ነገር አይደለም። በአጠቃላይ በነበረኝ ጊዜ ጥሩ ቆይታ ነው የነበረኝ ነገም ከነገወዲያም ሀገሬ የኔን ድጋፍ በምትፈልግበት ነገር ሁሉ ሀገሬን ለማገልገል ዝግጁ ነኝ።”

ስለ ወላይታ ድቻ

“ብዙ ጊዜ መሳይ እና ድቻ ከእኔ መታሰቢያነት በደንብ የተቆራኘ ነው። ከታናሽነቴ ጊዜ ጀምሮ አብረን ነው የነበርነው። ብዙ ውጣ ውረዶችን አስደሳች ጊዜያትን አሳልፈናል። አሁን ደግሞ ቡድኑ ችግር ውስጥ ነው ያለው። ከገባበት ችግር ውስጥ እንዲወጣ የምችለውን ሁሉ ለማድረግ ፣ ከሌሎችም ጋር አብሮ በመሥራት ካለበት ለማውጣት ጥሪውን ተቀብያለሁ። ይህ ኃላፊነት አሰልጣኝ ብቻውን ስለማይወጣው የሁሉም ትብብር ያስፈልጋል። ኑናራ ዲያጌ ኡባ ጦንያጋ ብያለሁ።”