ቅዱስ ጊዮርጊስ ካልተከፈለ ውዝፍ ዕዳ ጋር በተያያዘ የእግድ ውሳኔ ተላልፎበታል።
አንጋፋው ቅዱስ ጊዮርጊስ ካልተከፈለ የተጫዋች ውዝፍ ዕዳ ጋር በተያያዘ በዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማኅበር (FIFA) ዕግድ ተላለፈበት። “ያልተከፈለኝ ደሞዝ አለ” ብሎ ለፊፋ አቤቱታውን ያቀረበው ደግሞ ጋናዊው ፍሪምፖንግ ክዋሜ ሲሆን ጉዳዮን ሲመለከት የቆየው የፊፋ የዲሲፕሊን ኮሚቴም ቅዱስ ጊዮርጊስ ለተጫዋቹ ያልከፈለውን ደሞዝ ከፍሎ እንዲያጠናቅቅ ይህ ተፈፃሚ የማይሆን ከሆነ ደግሞ አሁን የተወሰነው የሦስት መስኮቶች የዝውውር እገዳ እንዲፀና እና የውሳኔውን ተፈጻሚነት ደግሞ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን እንዲከታተል በመጠቆም የዕግድ ውሳኔውን አሳልፏል።

በሀገሩ ክለቦች አሻንቲ ኮቶኮ እና አዱዋና ስታርስ እንዲሁም በስዊድኑ ክለብ ዳልኩርግ ከተጫወተ በኋላ ሐምሌ 28/2015 ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ያመራው አማካዩ ፍሪምፖንግ ክዋሜ በፈረሰኞቹ ቤት ለሁለት ዓመታት ቆይታ ማድረጉ ይታወቃል።


