በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ጠንካራ ተፎካካሪ የነበረው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ለቀጣዩ የውድድር ዘመን የሚጠቀምበትን ስብስብ አጠቃልሎ ወደ መጨረሱ ተቃርቧል።

ከሁሉም አስቀድመው ወደ ተፎካካሪነት ያሸጋገራቸውን አሠልጣኝ ኤርሚያስ ዱባለን ውል ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት ያራዘሙት ኢትዮ ኤሌክትሪኮች ስምንት ተጫዋቾችን ማለትም አጥቂዎቹ ታሪክ ጴጥሮስ እና ቤተልሔም መንተሎ ፤ አማካዮቹ ሲሣይ ገብረዋህድ ፣ ሚልዮን ጋይም እና ሂሩት ተስፋዬ ፤ ተከላካይዋ ብርቄ አማረ እና ግብ ጠባቂዋ አበባየሁ ጣሰው እና የመስመር ተጫዋቿ መሠረት ወርቅነህን በሁለት ዓመት ውል ያስፈረመው ኤሌክትሪክ ከዚህ በመቀጠል የ8 ተጫዋቾችን ውል ማደሱ ታውቋል።

ዳግማዊት ሰለሞን ፣ ኢየሩስ ወንድሙ ፣ ብርሃን ኃይለሥላሴ ፣ ገብርኤላ አበበ ፣ ፀጋነሽ ወራና ፣ ባንቺይርጋ ተስፋየ ፣ ቤተልሔም በቀለ ፣ ህድዓት ካሱ እና ትዕግስት ያደታ ደግሞ በክለቡ ለመቆየት ውላቸውን ያራዘሙ ተጫዋቾች ናቸው።

