ዓሊ አህመድ ከባድ ጉዳት አስተናግዷል

ዓሊ አህመድ ከባድ ጉዳት አስተናግዷል

የኖርዊች ሲቲው ትውልደ ኢትዮጵያዊው ተጫዋች ዓሊ አህመድ ከባድ ጉዳት አጋጠመው።

በቅርቡ የትውልድ ሀገሩን ኢትዮጵያ ጎብኝቶ የተመለሰው የኖርዊች ሲቲው መስመር ተጫዋች ዓሊ አህመድ በቀኝ ጉልበቱ ላይ በደረሰበት የጅማት መበጠስ (ACL) ከባድ ጉዳት ምክንያት ለረጅም ጊዜ ከሜዳ እንደሚርቅ ክለቡ ይፋ አድርጓል። የ25 ዓመቱ ዓሊ ባለፈው ቅዳሜ ኖርዊች ሲቲ በካሮው ሮድ በኦሳሱና 2 ለ 1 በተሸነፈበት የቅድመ ውድድር ዝግጅት ጨዋታ ሁለተኛ አጋማሽ ላይ በከባድ ሁኔታ በመውደቁ በህክምና ባለሙያዎች ታግዞ ከሜዳ ለመውጣት ተገዶ ነበር።

የክለቡ ዋና አሰልጣኝ ፊሊፕ ክሌመንት ጉዳቱ ከባድ መሆኑን የጠቆሙ ሲሆን ተጫዋቹ በዚህ ወር ቀዶ ጥገና እንደሚደረግለት እና የ2026-27 የውድድር ዘመን አብዛኛውን ወይም ሙሉውን ክፍል እንደሚያመልጠው ተረጋግጧል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የዓሊ አህመድ የቅርብ ጓደኛ እና የቡድን አጋሩ ሞ ቱሬ ለተጎዳው አጋሩ ያለው ወዳጅነት እና ድጋፍ ለማሳየት የነበረውን የጀርባ ቁጥር 37 ወደ አሊ አህመድ ቁጥር 21 ለመቀየር ያቀረበው ጥያቄ በክለቡ ጸድቆለታል።