ያሬድ መሐመድ በአዲስ አዳጊዎቹ ቤት ይቆያል

ያሬድ መሐመድ በአዲስ አዳጊዎቹ ቤት ይቆያል

ከሀላባ ከተማ ጋር ጥሩ ጊዜ ያሳለፈው ሁለገቡ ተጫዋች ውሉን አራዝሟል።

በአሰልጣኝ በሽር አብደላ የሚመሩት አዲስ አዳጊዎቹ ሀላባ ከተማዎች እስካሁን በዝውውሩ አሳዲስ ተጫዋቾቸን በማምጣት እና ቡድኑ ወደ ፕሪሚየር ሊግ እንዲያድግ ወሳኝ ሚና የነበራቸውን ተጫዋቾችን ውል እያራዘመ ይገኛል። አሁንም የመስመር ተከላካዩ ያሬድ መሐመድን ውል ማራዘማቸውን አውቀናል።

በሀዋሳ ተስፋ ቡድን መጫወት የጀመረው ያሬድ በ2017 ወደ ኢትዮጵያ መድን በመምጣት በአብዛኛው ጨዋታዎች ላይ ተሳትፎ ባያደርገም ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ በማሳየት ቡድኑ የሊጉን ዋንጫ ሲያነሳ አብሮ ነበር። ዘንድሮ በከፍተኛ ሊጉ ሀላባ ወደ ሊጉ እንዲያደግ በቡድኑ ውስጥ ከነበሩ ወሳኝ ተጫዋቾች መካከል አንዱ የነበረ መሆኑን ተከትሎ ለተጨማሪ ዓመት ከቡድኑ ጋር እንዲቆይ ተደርጓል።