ኢትዮጵያ መድን የመስመር ተጫዋች አስፈረመ

ኢትዮጵያ መድን የመስመር ተጫዋች አስፈረመ

ብሩንዳዊው ተጫዋች ኢትዮጵያ መድንን ተቀላቀለ።

ቀደም ብለው የመስመር ተጫዋቹ ሳሙኤል ሳሊሶን ለማስፈረም የተስማሙት ኢትዮጵያ መድኖች አሁን ደግሞ ብሩንዳዊው አልፍሬድ ንኩሩንዚዛን አስፈርመዋል። በ ‘Aigle Noir’ ካሳለፈው አንድ የውድድር ዓመት ውጭ የተቀረውን የእግር ኳስ ሂወቱ በአሳዳጊ ክለብ ቡማሙሩ ያሳለፈው ይህ የመስመር ተጫዋች በውድድር ዓመቱ ስምንት ግቦች ማስቆጠር የቻለ ሲሆን በብሩንዲ ፕሪምየር ሊግ ትልቅ ተስፋ ከሚጣልባቸው ተስፈኛ ተጫዋቾች አንዱ ነበር።