ምዓም አናብስት የዝውውር መስኮቱ የመጀመሪያ ፈራሚያቸው ለማግኘት ተቃርበዋል

በሀያ ሁለት ነጥብ 18ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡት
መቐለ 70 እንደርታዎች የዝውውር መስኮቱ የመጀመሪያ ፈራሚያቸው ለማግኘት ከስምምነት ደርሰዋል። ወደ ቡድኑ ለመቀላቀል ከስምምነት የደረሰው ደግሞ አማካዩ ሀብታሙ ንጉሴ ነው። ከዚህ ቀደም በባህር ዳር ከተማ ፣ ወልዲያ ከተማ፣ መቐለ 70 እንደርታ፣ ጅማ አባ ጅፋር፣ ወላይታ ድቻ፣
ሻሸመኔ ከተማ እና በወልዋሎ ቆይታ የነበረው ተጫዋቹ ላለፉት ቀናት ከቡድኑ ጋር ልምምድ በመስራት ላይ የቆየ ሲሆን መቐለ 70 እንደርታን ለመቀላቀል መስማማቱን ተከትሎም በቀጣይ ቀናት በይፋ ፌርማውን ያኖራል ተብሎ ይጠበቃል።

