አሰልጣኝ ገብረመድህን ሀይሌ የሰጡት ምላሽ ..?

አሰልጣኝ ገብረመድህን ሀይሌ የሰጡት ምላሽ ..?


👉 “የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊን ይዤ የማይሳካ ነገር አይኖርም

👉 “በስራዬ ምንም አይነት ጣልጋ ገብነት የለም”

👉” ስናቅድ ቻምፕዮን እንሆናለን ብለን አቅደናል። ከሰራን ይሳካል ..”

አሰልጣኝ ገብረመድህን ሀይሌ ኢትዮጵያ ቡናን ለሁለት ዓመት ለማሰልጠን መስማማታቸውን ተከትሎ ይፋዊ የፊርማ ስነ ስርዓት እና ጋዜጣዊ መግለጫ በስካይ ላይት ሆቴል ተካሂዷል። ዋና አሰልጣኙ ያደረጉትን የመግቢያ ንግግራቸውን አስቀድመን ያጋራናቹህ ሲሆን አሁን ደግሞ ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የሰጡትን ምላሽ ይዘን ቀርበናል።

ኢትዮጵያ ቡናን ቻምፕዮን ስለ ማድረግ ?

ኢትዮጰያ ቡና እንደሚታወቀው የብዙ ደጋፊ ባለቤት ነው። ቻምፕዮን ከሆነ አስራ አምስት ዓመታት ሆኖታል። ቻምፕዮን የመሆን ዕድሉን ደግሞ ከዚህ ሁሉ ደጋፊ ጋር ሆኖ ማሳካት ይቻላል። የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብን ውጤታማ ማድረግ ተቀዳሚ አላማዬ ነው ፤ የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊና በዚህ ልክ ከፍተኛ ፍላጎት ያለው አመራር ይዘን በጋራ ይህንን ማሳካት እንችላለን። እናቅዳለን ፤ እናሳካለን።”

ክረምት ላይ ሁሌ ዋንጫ ይታቀዳል ግን አይሳካም ዘንድሮስ ይሳካል ?

“አዎ ይሳካል! ከዛም በላይ መሄድ ይቻላል። የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊን ይዤ የማይሳካ ነገር አይኖርም። ኢትዮጵያ ቡና ደጋፊ ጥሩ ነገር ከሰራህለት ጥሩ ምላሽ የሚሰጥ ደጋፊ ነው ፤ ይህን የደጋፊ አቅም ይዘህ የማይሳካ ነገር አይኖርም።”

የክለቡን ጫና ስለመቋቋም ?

ስናቅድ ቻምፕዮን እንሆናለን ብለን አቅደናል። ከሰራን ይሳካል። እኔ ባይሆንስ የሚለው አባባል ብዙም አይታየኝም። ዕቅድህን ባመዛኙ ማሳካት ከቻልክ ወደ ሁለተኛ አማራጭ የምትሄድበት ነገር አይኖርም። ይህን ከልቡ ክለቡን እየተዟዟረ የሚደግፍ ደጋፊ አቅም ይዘህ የማይሳካ ነገር አይኖርም።”

ከቦርዱ ለምትሰራው ስራ ተመቻችቶልሀል ?

“አዎ ተመቻችቶልኛል.. በቅድሚያ ከአመራሩ ጋር ስንነጋር ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ረዘም ላለ ጊዜ ተነጋግረናል ፤ ስለዚህ ጥሩ ነገር ለመስራት የሚያስችል ሁኔታ አሁን በክለብ ውስጥ አለ። ሁላችንም የድርሻችን ከተወጣን የምናሳካው ነገር አይኖርም።

ጣልቃ ገብነት አለ ?

“በስራዬ ምንም አይነት ጣልጋ ገብነት የለም። እኔ በሰራውባቸው ክለቦች የሙያ ነፃነቴን አሳልፌ አልሰጥም።ከአመራሮቹ ጋር መጀመርያ የተነጋገርንባቸው በዚህ ጉዳይ ነው። ደጋፊ የደጋፊነቱን ይሰጥሀል። አመራሩ ደግሞ በተለያዮ መንገድ ይደግፋል። እኛ ደግሞ ቴክኒካል ነገሮች እንሰራለን ማለት ነው።