ሲዳማ ቡና የመስመር አጥቂውን ውል ለማራዘም ከስምምነት ደርሷል
የ2018 የሊጉ አሸናፊ በመሆን ሀገራችንን በአፍሪካ መድረክ የሚወክለው ሲዳማ ቡና ለቀጣይ ዓመት ራሱን ለማጠናከር ወደ ዝውውሩ በመግባት የመስመር አጥቂውን መስፍን ታፈሰን ውል ለማራዘም ከስምምነት መድረሱን አውቀናል።

ከሀዋሳ ታዳጊ ቡድን እስከ ዋናው ቡድን በመጫወት የእግርኳስ ህይወቱን የጀመረው ፈጣኑ የመስመር አጥቂ በኢትዮጵያ ቡና ቆይታ ካደረገ በኋላ ያለፉትን ሁለት ዓመታት በሲዳማ ቡና ቆይታ በማድረግ ቡድኑ የሊጉን ዋንጫ እንዲያሳካ ትልቁን ሚና መወጣቱ ሲታወስ አሁን ደግሞ ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት በሲዳማ ቡና የሚያቆየውን ውል ለማራዘም መስማማቱን ታውቋል።
ሲዳማ ቡና በቀጣዮቹ ቀናት ተጨማሪ ዝውውር እንደሚፈፅም ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።

