አማካዩ ከክለቡ ጋር አይገኝም

አማካዩ ከክለቡ ጋር አይገኝም

የመቐለ 70 እንደርታው አማካይ አብርሃም ጌታቸው ከክለቡ ጋር አብሮ እንደማይገኝ ሰምተናል

በዘንድሮ ውድድር ዓመት መቐለ 70 እንደርታን ተቀላቅሎ ክለቡን በማገልገል ላይ የነበረው አብርሃም ጌታቸው ከክለቡ ጋር አይገኝም። ተጫዋቹ በአሁኑ ወቅት በዩናይትድ ስቴትስ የሚገኝ ሲሆን በተጨማሪም ከክለቡ እውቅና ውጭ ወደ ሀገሪቱ እንዳቀና አውቀናል።

አብርሃም በቅዱስ ጊዮርጊስ ከታዳጊ ቡድን አንስቶ እስከ ዋናው ቡድን ድረስ መጫወት የቻለ ሲሆን በእግርኳስ ህይወቱ ሁለተኛ ወደ ሆነው ክለብ መቐለ 70 እንደርታ ተቀላቅሎ ላለፉት ስድስት ወራት ቆይታ ካደረገ በኋላም ባልታወቀ ምክንያት ወደ ዩናይትድ ስቴስት አምርቷል። በዚህ ጉዳይ ዙርያ ተጨማሪ ምላሾችን ለማግኘት ተጫዋቹም ሆነ ክለቡ ለማግኘት ጥረት እያደረግን ሲሆን መረጃዎችን እንዳገኘን የምንመለስበት ይሆናል።