የአብነት ደምሴ ጥያቄ ተቀባይነት አገኝ

የአብነት ደምሴ ጥያቄ ተቀባይነት አገኝ

በተጠናቀቀው ውድድር ዓመት ከሐይቆቹ ጋር ያሳለፈው አማካይ ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቷል

በ2017 መጨረሻ በሁለት ዓመት ውል ሐይቆቹን ተቀላቅሎ ከክለቡ ጋር የአንድ ዓመት ቆይታ ያደረገው አማካዩ አብነት ደምሴ ቀደም ብሎ ያቀረበው የልቀቁኝ ጥያቄ በሀዋሳ ከተማ ተቀባይነት አግኝቶ አንድ ዓመት ቀሪ ውል እያለው ዛሬ ከክለቡ ጋር ለመለያየት በቅቷል።

ከዚህ ቀደም በወላይታ ድቻ ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ፣ ኢትዮጵያ ቡና እና በሀዋሳ ከተማ መጫወት የቻለው ቁመተ መለሎው አማካይ ከአንድ ዓመት ቆይታ በኋላ ከሐይቆቹ ጋር መለያየቱን ተከትሎ በቀጣይ ማረፍያው ዙርያ ላቀረብንለት ጥያቄ በአሁን ሰዓት ለዕረፍት ወደ ትውልድ ቦታው እንዳቀናና በቀጣይ ስለ ቀጣይ ክለቡ እንደሚወስን ነግሮናል።