ኢትዮጵያ ቡናዎች አምስተኛ ፈራሚያቸው አግኝተዋል

ኢትዮጵያ ቡናዎች አምስተኛ ፈራሚያቸው አግኝተዋል

በብርቱካናማዎቹ ቆይታ የነበረው ተጫዋች ወደ ቡናማዎቹ ለማምራት ከስምምነት ደርሷል

ቀደም ብለው ግብ ጠባቂው አቡበከር ኑራ ፣ በረከት ወልደ ዩሐንስ ፣ አብዱልሰላም የሱፍ ፣ ሀብታሙ ተከስተ ለማስፈረም ተስማምተው የነባሮቹ አማኑኤል አድማሱ ፣ ይታገሱ ታሪኩ ፣ ኤርምያስ ሹምበዛ እና ረጂብ ሚፍታሕን ውል ለተጨማሪ ዓመት ለማራዘም የተስማሙት ኢትዮጵያ ቡናዎች አሁን ደግሞ ላለፉት ዓመታት በድሬዳዋ ከተማ ቆይታ ያደረገውን ተከላካዩ ድል አዲስ ገብሬ ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል።

በታዳጊነት ጊዜው በመቻል እና አዲስ አበባ ከተማ ከ20 ዓመት በታች ቡድኖች ውስጥ ተጫውቶ ያሳለፈው ድልአዲስ ቀጥሎም የከፍተኛ ሊጎቹ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ እና ሰሜን ሸዋ ደብረብርሃን እንዲሁም ያለፉትን ሁለት ዓመታት በድሬዳዋ ከተማ መጫወቱ መጫወቱ የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ ቡና ለማምራት ከስምምነት ደርሷል።